Quantcast
Channel: Horn of Africa
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2469

Two Loyal Ethiopian journalists ask for political asylum in the U.S. and another in Sweden

$
0
0

Ameha-Fessha(The Ethiopian Observer) — A senior sports journalist working for the Addis Ababa Mass Media Agency and another reporter for the state-run news agency, ENA have requested political asylum in the U.S., according to reliable sources.

The journalists, Ameha Fessha and Libanos Yohannes headed to the United States on March to cover the 16th IAAF World Indoors Athletics championships from march 17-20 Portland Oregon IAAF World Indoor Championships Portland 2016. The two journalists decided to remain there and colleagues informed Ethiopia Observer that the journalists have asked asylum by claiming there is no freedom of expression in Ethiopia during the last few days.
In a related news, the reporter for the government-affiliated Fana Broadcasting Corporate Thomas Sebsebe, has also asked asylum in Sweden, it has emerged. The reporter who went there to cover the Stockholm Diamond League on May 30 told friends that he is asking for political asylum in Sweden.

Ethiopia is one of the top countries from which journalists flee. The majority of those journalists hailed from independent media outlets, but it is not uncommon to see journalists working for the government asking for asylum.


በሰንዳፋ በአንድ ቢሊዮን ብር በተገነባው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ መጠቀም ተከለከለ

#‎OromoProtests‬ This is another victory for the Oromo farmers. Finfinnee, since its establishment 130 years ago, served & is serving nothing good to Oromia excepting dumping its waste, every waste, on it. When the architects of the current federal structure sliced Finfinnee out from Oromia through a legal fiction, they knew that, for sure, the city shall run out of land to face such a problem sometime in the future. But they didn’t care. Alas!

VIVA Qunnaan bultoota Oromoo. Akkauma dhiiraa ufirraa dhowwitan balfa isaanii via Girma Gutema

‹‹ለጊዜው ሌሎች ማጠራቀሚያዎች እየፈለግን ነው›› የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ

front1693

(Ethiopian Reporter) — ለደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተገንብቶ በታኅሳስ ወር 2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት ጀምሮ የነበረው ‹‹ሰንዳፋ ሳኒተሪ ላንድ ፊል›› ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ፣ ከአዲስ አበባ ከተማ እየተወሰደ የሚደፋው ቆሻሻ እንዳይወገድ ተከለከለ፡፡
አገልግሎት መስጠት ከጀመረ ሰባት ወራት እንዳስቆጠረ በተገለጸው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ ቆሻሻ እንዳይጣል የከለከሉት፣ በአካባቢው የሚገኙ አርሶ አደሮች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳዊት አየለ ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ በኦሮሚያ ክልል ከካራ በ40 ኪሎ ሜትር ርቀት ሰንዳፋ በተገነባው ዘመናዊ የደረቅ ቆሻሻ ገንዳ ውስጥ የአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻ እንዳይጣል የከለከሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ናቸው፡፡ በመሆኑም ከሐምሌ 7 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ የአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻን ወደዚያ መውሰድ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የኦሮሚያ ክልል የሚመለከተው የአስተዳደር አካል በጉዳዩ ላይ የተወያዩ ቢሆንም፣ ስምምነት ላይ አለመደረሱን ከዋና ዳይሬክተሩ ለመረዳት ተችሏል፡፡
ላለፉት ሰባት ቀናት የአዲስ አበባ ደረቅ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች ሞልተው በመፍሰስ ላይ ሲሆኑ፣ የክረምት ወቅት በመሆኑ ምክንያት ከገንዳ ተርፎ የሚፈሰው ቆሻሻ በዝናብ ውኃ እየታጠበ ስለሚፈስ ነዋሪዎች ሥጋት ውስጥ መሆናቸውን እየገለጹ ነው፡፡
በየካቲት 12 ሆስፒታል አካባቢ ነዋሪ የሆኑት አቶ ግርማቸው አሰፋ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በአካባቢው ያሉት ገንዳዎች በየቀኑ በደረቅ ቆሻሻ ይሞላሉ፡፡ ‹‹በአካባቢው ሆስፒታል ያለ በመሆኑም፣ ደረቅ ቆሻሻ የሚያነሱ ተሽከርካሪዎች ቶሎ ቶሎ እየመጡ ያነሱ ነበር፡፡ በገንዳዎቹ ውስጥ በተለያዩ ምክንያቶች የሞቱ እንስሳት፣ ፈርስና ከፍተኛ መርዝነት ያላቸው ኬሚካሎች ጭምር ስለሚደፉ ገንዳዎቹ ከአንድ ቀን በላይ መቆየት አይችሉም፤›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን ላለፉት ስድስት ቀናት ገንዳዎቹ ባለመነሳታቸው በአካባቢው መተላለፍ አለመቻሉን አስረድተዋል፡፡
አቶ ግርማቸው እንደገለጹት ሁሉ በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ቦታዎች የተቀመጡ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳዎች በመሙላታቸው፣ ነዋሪዎች በመጥፎ ሽታ እየተቸገሩ መሆኑን በምሬት እየተናገሩ ነው፡፡
የከተማው ነዋሪዎች እንደሚናገሩት ችግሩ የተፈጠረበት ወቅት ክረምት ከመሆኑ አንፃር ሥጋታቸው የተደራረበ ነው፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በየቀኑና በየሰዓቱ ከአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) ነዋሪዎች መጠንቀቅ እንዳለባቸው፣ አካባቢያቸውን ማፅዳትና በንፅህና መጠበቅ ግዴታቸው ጭምር መሆኑን እየገለጹ ባለበት ወቅት፣ አስተዳደሩ ያስቀመጣቸው ገንዳዎች አለመነሳታቸው ሥጋታቸውን ከፍ እንዳደረገው እየተናገሩ ነው፡፡
የከተማ አስተዳደሩም ሆነ መንግሥት ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው ለሕዝቡ ጤንነት በመሆኑ፣ አፋጣኝ መፍትሔ መፈለግና የተጠራቀሙት ቆሻሻዎች መነሳት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ስለታሰበው መፍትሔ ተጠይቀው፣ ‹‹ሌሎች አማራጮችን እየፈለግን ነው፡፡ አቃቂ ቃሊቲ አካባቢና ሌሎች አካባቢዎችንም እያየን ነው፤›› ብለዋል፡፡
አርሶ አደሮቹ ለምን እንደከለከሉና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር ስምምነት ላይ ያልተደረሰበትን ምክንያት የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ ዝምታን መርጠዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ከተማ በቀን 2,400 ቶን ወይም 8,050 ሜትር ኪዩብ ቆሻሻ ወደ ማጠራቀሚያ ገንዳ ይወሰድ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2469